በአዲስ መልክ በለማው ድረ-ገጽ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጠ Post author:በፍቃዱ ከፈለኝ Post published:October 25, 2021 Post category:Uncategorized በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በአዲስ መልክ ባለማው ድረ-ገጽ ዙሪያ ለማኔጅመንት አባላት ማክሰኞ ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም ማብራሪያ ሰጠ፡፡ማብራሪያውን አቶ ቴዎድሮስ ወርቁ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ባቀረቡበት ወቅት ድረ-ገጹን በአዲስ መልክ ማልማት ያስፈለገበትን ምክንያት፣ ያካተታቸውን ተጨማሪ ይዘቶችና ቋንቋዎች ወዘተ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ የማኔጅመንት አባላቱም ለተከናወነው ተግባር ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ለቀረቡ የማብራሪያ ጥያቄዎች መልስ በመስጠት ፕሮግራሙ መጠናቀቁን መረዳት ተችሏል፡፡ ተጨማሪ ዜናዎች የህዳር ወር ሳይንሳዊ ሴሚናር ተካሄደ December 10, 2021 ዓለም አቀፍ የብዝሀ ሕይወት ቀን በዓል በክልል ደረጃ ተከበረ June 13, 2022 ወርሀዊ ሳይንሳዊ ሴሚናር ቀረበ October 25, 2021