You are currently viewing Tablet applications were developed

የታብሌት አፕሊኬሽኖች ተዘጋጅተው ለአገልግሎት በቁ

በኢትዮጵያ ብዝሀ ሕይወት ኢንስቲትዩት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት በመስክ ላይ መረጃ መሰብሰብ የሚያስችሉ ሀያ ስድስት አፕሊኬሽኖችን አዘጋጅቶ ስልጠና በመስጠት ለአዝርዕትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት ጥቅምት 04 ቀን 2014 ዓ.ም አስረከበ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ አቶ ውብሸት ተሾመ የአዝርዕትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ስልጠናውን በአግባቡ በመውሰድ ወደ ተግባር መለወጥ ይጠበቅባችኋል የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

አፕሊኬሽኖቹ የተዘጋጁት በአዝርዕትና ሆርቲካልቸር ብዝሀ ሕይወት ዳይሬክቶሬት ጥያቄ መሰረት መሆኑን አቶ ቴዎድሮስ ወርቁ የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የጠቀሱ ሲሆን ስልጠናው በዳታቤዝ ባለሙያ የምስራች ስዩም ቀርቧል፡፡ የተግባር ስልጠና ተሰጥቶ ፕሮግራሙ መጠናቀቁን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዘግቧል፡፡